የዓለማቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት ተወካዮች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
· Visiting
A delegation from the International Telecommunication Union led by Cosmas Zavazava visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to explore collaboration opportunities in AI research, digital infrastructure, and capacity building.
በዓለማቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት የቴሌኮሙኒኬሽን ልማት ቢሮ ዳይሬክተር (ዶ/ር) ኮስማስ ዛቫዛቫ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ስለ ኢንስቲትዩቱ የምርምር ተግባራት፣ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ስለተሰሩ ፕሮጀክቶች እና ኢንስቲትዩቱ ዲጂታላይዜሽንን ለመደገፍ ስላለው ሚና ለጎብኚዎቹ አብራርተዋል።
ጉብኝቱን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት ኮስማስ ዛቫዛቫ (ዶ/ር) በኢንስቲትዩቱ ውስጥ ለሚከናወነው የቴክኖሎጂ ስራ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። ኢንስቲትዩቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር እና ፈጠራን በማሳደግ ረገድ ጠንካራ አቅም እንዳለው መመልከታቸውን ተናግረዋል። አክለውም ዓለማቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በምርምር እና በአቅም ግንባታ ዘርፍ አብረው ለመስራት ተስፋ ሰጪ እድሎች እንዳሉ ተናግረዋል።
ከጉብኝቱ በተጨማሪ በኢትዮጵያ እና በመላው አፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ፈጠራን የሚደግፍ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ተደርጓል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute