የሚኒስትሮች ምክር ቤት የብሔራዊ ዳታ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ
· Other
Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption Commission Explores AI Solutions to Improve Efficiency, Transparency, and Anti-Corruption Efforts
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 59ኛ መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ የዳታ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ላይ በሰፊው ተወያይቶ እና ግብአቶችን
በማከል ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
ረቂቅ አዋጁ የተዘጋጀው የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግቦች ለማሳካት ነዉ። በተጨማሪም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምርና የፈጠራ አቅምን ለማጎልበት፣ የኢኖቬሽንና የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን እና በዳታ የተመራ የኢኮኖሚ ልማት ሥርዓት ለመገንባት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
የዳታ ደህንነትንና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የዳታ መጋራትን፣ የዳታ ተናባቢነትንና የዳታ መልሶ አጠቃቀምን በማጠናከር የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማዘመን ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቷል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute