የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስታርታፕ ሥነ-ምህዳሩን ለማነቃቃት ከአሀዱ ባንክ እና ከኤ.ኤል.ኤክስ (ALX) ጋር ተባብሮ ለመስራት ተስማማ
· MOU
EAII Signs MoUs with Ahadu Bank and ALX Ethiopia to Boost AI Startups, Talent Development, and National Productivity
የኢትዮጵያአርቲፊሻል ኢንተለጀንስኢንስቲትዩት በሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ስታርታፖችን ለመደገፍናየሰው ኃይል ልማትን ለማፋጠን የሚያስችሉ የመግባቢያ ስምምነቶችን ከአሀዱ ባንክእና ከአፍሪካ ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት (ALX ኢትዮጵያ) ጋር ተፈራርሟል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢንስቲትዩቱዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በአፍሪካ በአይነቱ ልዩ የሆነ የኤ.አይስታርታፕ ማዕከል በማቋቋም ለማነቃቃትበምትሰራው ስራ ከግልተቋማት ጋር መሰልትብብሮች መደረጋቸውወሳኝ ነው ብለዋል።ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ ያለውን የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ
የማስተማርናየማሰልጠን ስራዎችን በስፋት ሲያከናውን መቆየቱንምዋና ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል።
የአሀዱ ባንክዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶሙሉጌታ በዛ በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ በስታርታፖችላይ እያከናወነ የሚገኘው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው፤ ስምምነቱ የባንኩን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ከማጎልበትባለፈ ለተቋሙ ውጤታማነትትልቅ አጋዥ እንደሚሆንተናግረዋል።
የኤ.ኤል.ኤክስ (ALX) ኢትዮጵያ ዋና ሥራአስፈጻሚ ምዕራፍ ገብረማርቆስ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት እንደገለጹት፥ ስምምነቱ ቀደምሲል የተጀመሩ ስራዎችን
ወደላቀ ደረጃ የሚያሸጋግርመሆኑን ጠቁመዋል።ተቋማቸው በስታርታፕሥነ-ምህዳር ላይ ያለውን ዓለማቀፋዊ ልምድ ለኢትዮጵያ የሚያጋራበት መልካም
አጋጣሚ መፈጠሩንም ገልጸዋል።
ይህ የጋራትብብር በኢትዮጵያየኤ.አይ ቴክኖሎጂ ፈጠራእንዲስፋፋ፣ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ተቋማት የፋይናንስናየቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኙ እንዲሁም ዓለማቀፍ ተወዳዳሪነት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute