የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አደረጉ፡፡
· Visiting
Officials from Adama Science and Technology University led by Lemi Guta visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to strengthen collaboration in AI research, education, and innovation.
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር) የተመራ የልዑካን ቡድን በኢንስቲትዩቱ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርጓል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ለልዑካን ቡድኑ የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡
የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር) በኢንስቲትዩቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እና ሀገራችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መስክ ምን እየሰራች እንዳለ ብሎም ወደየት እየተጓዘች እንደሆነ በጉብኝቱ ማየት እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡
ጉብኝቱ በሁለቱ ተቋማት ትብብር እየተሰሩ የሚገኙ የጥናት እና ምርምር ስራዎችን ለማስፋት እንዲሁም በማስተርስ እና በሶስተኛ ዲግሪ እየተሰጠ ያለውን የኤ.አይ ትምህርት ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute