ሂውማን ኢን ዘሉፕ (Human-in-the-Loop (HITL) ምንድነው?
· Other
Human-in-the-Loop Combines AI Efficiency with Human Expertise, Ethical Judgment, and Oversight in High-Risk Decisions
ሂውማን ኢን ዘሉፕ(HITL) ማለት የሰው ልጅ በኤ.አይ ሥርዓት ውስጥ በንቃት የሚሳተፍበት አሠራር ነው። ይህም ኤ.አይ ብቻውን ውሳኔ እንዲወስን ከመተው ይልቅ የሰው ልጅ የኤ.አይ ውጤትን እንዲመረምር፣ እንዲያርም፣ እንዲያጸድቅ ወይም አስፈላጊ ሲሆን ውሳኔውን እንዲሽር ያስችላል።
ለምሳሌ ኤ.አይ የሕክምና ምስልን በመመርመር ችግር ሊኖር የሚችልበትን ቦታ ሊጠቁም ይችላል የመጨረሻውን ግምገማ ግን የህክምና ባለሙያዎች ነው። ኤ.አይ ለፍጥነትና መረጃ ለመተንተን ሲውል ሰው ደግሞ ሙያዊ ዕውቀቱን፣ ስነምግባራዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነቱን እንዲጠቀም ዕድል የሚሰጥ አሰራር ስለመሆኑ የአይ.ቢ.ኤም ድረገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡
በኤ.አይ ሥርዓት ሥልጠና ወቅት ሰዎች መረጃን ሊመድቡና ሊያስተካክሉ ይችላሉ፤ ለአብነት ምስሎችን“ጤናማ” ወይም“ችግር ያለበት” ብለው በመለየት ኤ.አይ ከምሳሌዎቹ እንዲማር ያግዛሉ።በዚህም በተለይ በጤና፣ በፋይናንስ፣ በሕዝብ አገልግሎትና ሰውን በቀጥታ ሊነኩ በሚችሉ ውሳኔዎች ላይ ጠቃሚ ነው።
በመሆኑም ሂውማን ኢን ዘሉፕ ማለት ኤ.አይ ሰውን ሙሉ በሙሉ የሚተካበት ሳይሆን፣ ኤ.አይ እና የሰው ልጅ በተለያዩ የሥራ ደረጃዎች ተባብረው የሚሠሩበት አሠራር ነው። የአውሮፓ ሕብረት ኤ.አይ አክት ከፍተኛ ስጋት ባለባቸው የኤ.አይ ሥርዓቶች ተገቢ የሰው ቁጥጥር እንዲኖር ይደነግጋል።
የሰውልጅተሳትፎ የኤ.አይ ውጤትን ለመረዳት፣ ለመቆጣጠር እና አስፈላጊ ሲሆን ጣልቃ ለመግባት ተጨባጭ ሥልጣን የሚሰጠው መሆን እንደሚገባም
ይገልጻል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute