“ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው መስክ ያላትን አቅም እያሳየች ነው፡፡” በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ
· Visiting
U.S. Ambassador Ervin Masinga Highlights Ethiopia’s Growing Technological Potential and Its Role in Driving Economic Growth and Productivity
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ኤርቪን ማሲንጋ እና ልዑካቸው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ለልዑካኑ የኢንስቲትዩቱን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ
ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡
ጉብኝቱን አስመልክቶ ሀሳባቸውን የገለጹት አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እየሰራ ያለው ስራ ሁሉንም መስኮች
መለወጥ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው መስክ ወደኋላ እንደማትቀር እያሳየች ትገኛለች ብለዋል፡፡ በኢንስቲትዩቱ የተመለከቱት ነገር ከጠበቁት በላይ እንደሆነ የገለጹት
አምባሳደሩ፤በሀገሪቱ ውስጥ በዘርፉ እምቅ አቅም እንዳለ የኢንስቲትዩቱ እንቅስቃሴ በሚገባ የሚገልጽ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ ይህንን ግንኙነት ወደ ግል ዘርፉም በማውረድ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
በምንገኝበት ዘመን የዓለም ኢኮኖሚ በዳታ ላይ መሰረት ያደረገ መሆኑን የተናገሩት አምባሳደሩ የዳታ ጉዳይ ትኩረት የሚሻ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡
ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ስትራቴጂካዊ አጋርነት እና የትብብር መስኮችን አስመልክቶ ውይይት ተደርጓል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute