‘’የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ራዕዩን ከ2030 ቀድሞ ለማሳካት የሚያስችለውን ስራዎች እየሰራ ነው፡፡’’ ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ
· Visiting
Bio and Emerging Technology Institute Delegation Visits EAII to Strengthen Innovation Collaboration and Digital Transformation
የባዮ እና ኤመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች እና ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ የቴክኖ
ስራዎችን ተመልክተዋል።
የባዮ እና ኤመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎች የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ ራዕይ ለማሳካት የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል። በተለይም ምርምሮች በወረቀት ላይ ብቻ ሳይወሰኑ ለተግባራዊ ውጤት እየበቁ መሆናቸው የሚያስመሰግን መሆኑን ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን እውን ለማድረግ ተቋማት በትስስር መስራታቸው ወሳኝ መሆኑን በመጠቆም ሁለቱ ተቋማት ወደፊት በጋራ እንደሚ ሰሩ አረጋግጠዋል።
ልዑካን ቡድኑ በጉብኝታቸው ወቅት የኢንስቲትዩቱን የኤ.አይ እና ሮቦቲክስ ማምረቻ ወርክሾፕ፣ የምርት ማሳያ ክፍል እንዲሁም የስታርታፕ ማዕከልን ተዘዋ
ውረው ተመልክተዋል። በየክፍሎቹም የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች ስለተሰሩት የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና ስላላቸው ፋይዳ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute