የአፍሪካ ንግድ ትምህርት ቤቶች ማህበር ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
· Visiting
International Delegates Commend EAII’s AI Vision and Data Infrastructure for Advancing Africa’s Digital Sovereignty and Productivity.
የጉባኤው ተሳታፊዎች በጉብኝታቸው ወቅት በኢንስቲትዩቱ የተመለከቱት የቴክኖሎጂ አቅምና ራዕይ ከጠበቁት በላይ እንደሆነ ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ እያከናወነ ያለው ተግባር ስኬታማና ተስፋ ሰጪ መሆኑን የገለፁት ተሳታፊዎቹ፤ በተለይም የዳታ ሴንተር ግንባታና የዳታ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እየተከናወነ ያለው ተግባር ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ የዳታ ሉዓላዊነት ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።
ተቋሙ ሰዎች ስለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ስለ ሮቦቲክስና ስለ ዘመኑ ቴክኖሎጂዎች የሚማሩበትና የሚወያዩበት ማዕከል ጭምር መሆኑን አድንቀዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ፉክክር ባለበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ እንዲህ ያለ ጠንካራ ብሔራዊ ተቋም መገንባቷ ለአፍሪካ አህጉር ትልቅ ትርጉም
እንዳለው የጉባኤው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
ኢንስቲትዩት ለስታርታፖች የሚሰጠውን ድጋፍ በተመለከተ እንዲሁም በሮቦቲክስና በሌሎችም ዘርፎች በሚሰራቸው ስራዎች ዙሪያ በኢንስቲትዩቱ አመራሮች ለጎብኚዎቹ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
በክቡር ኮሌጅ አዘጋጅነትየአፍሪካ ንግድ ትምህርት ቤቶች ማህበር (AABS) ጉባኤ ከ30 በላይ ሀገራት የተውጣጡ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች፣ ተመራማሪዎችና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከግንቦት 5-7፣2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute