”ኢትዮጵያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የልህቀት ማዕከል ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነት አድንቄያለሁ” አምባሳደር ማግኑስ ሌናርትሰን
· Visiting
Magnus Lennartsson, Ambassador of Sweden to Ethiopia, visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to explore collaboration opportunities in AI innovation, research, and digital infrastructure.
በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ማግነስ ሌናርትሰን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) አምባሳደሩና ልዑካቸውን ተቀብለው ኢንስቲትዩቱ ስለሚሰራቸው ስራዎች ገለፃ አድርገዋል። በገለፃቸውም ኢንስቲትዩቱ ኤ.አይን በመጠቀም ያለማቸውን ሲስተሞችና በዳታ ሴንተሩ በኩል ለተለያዩ የግልና የመንግስት ተቋማት እየሰጠ ስላለው የክላውድ አገልገሎት አብራርተዋል።
አምባሳደር ማግነስ ሌናርትሰን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የላቀ የብቃት ማዕከል ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነት በማድነቅ፤ በኢንስቲትዩቱ እየተከናወኑ ባሉ የፈጠራ ስራዎች እና በተለይም በስታርታፕ ማዕከሉ በርካታ ባለተሰጥኦ ወጣት ኢትዮጵያውያን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እየሰሩ የሚገኘው የፈጠራ ስራ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል።
በጉብኝቱ ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል በዘርፉ ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። አምባሳደሩ ይህን አስመልክቶ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ እና ስዊድን በፍጥነት እያደገ ባለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መስክ በግል ዘርፍ እና በተለይም በአካዳሚክ ጉዳዮች ትብብር በኩል በተቋማዊ መንገድ ለመተባበር ብዙ እድሎች እንዳሉ አመላክተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute