በሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኤ.አይ ክበብ ተቋቋመ።
· Education
EAII Launches AI Club at Sabian High School to Enhance Students’ Skills in Artificial Intelligence
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው ሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የኤ.አይ ክበብ አቋቁሟል።
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ክበቡ ስለኤ.አይ ቴክኖሎጂ ማወቅ ለሚፈልጉ ተማሪዎች መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል። ኢንስቲትዩቱ ተማሪዎቹ በዘርፉ ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችላቸውን ስልጠና እና ድጋፍ ለማቅረብ ዝግጁ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።
የሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህር አለም ታዬ የክበቡ አባላት ቀደም ሲል የ5 ሚልዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን እንዳጠናቀቁ ገልጸዋል። በክበቡ በሚኖራቸው ተሳትፎ ስለኤ.አይ ቴክኖሎጂ የበለጠ ዕውቀት የሚያገኙበት እንደሚሆንም ተናግረዋል።
በድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ የክበባት አስተባባሪ አቶ አስቻለው ሸዋረጋ በድሬዳዋ ከተማ የተከፈቱትን የኤ.አይ ክበባት በማቀናጀት በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute