“ኢትዮጵያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያዳርጋትን አቅም አጎልብታለች፡፡” የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ም/ዋና ፀሐፊ ሙሐመድ አብዲ ዋሬ
· Visiting
A high-level IGAD delegation led by Deputy Executive Secretary Mohamed Abdi Ware visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to explore regional cooperation, experience sharing, and the adoption of AI across key socio-economic sectors in IGAD member countries.
የምሥራቅ አፍሪካ ልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ም/ዋና ፀሐፊ ሙሐመድ አብዲ ዋሬ የተመራ ከፍተኛ የልዑክ ቡድን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል
ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የመስክ ጉብኝት አድርጓል። ሁሉን አቀፍ እድገት ለማስመዝገብ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወሳኝ ነው ያሉት ም/ዋና ፀሐፊው
ሙሐመድ አብዲ ዋሬ ኢትዮጵያ በሰው ኃይል ልማት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም ቴክኖሎጂውን በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት እና በፋይናንስ ዘርፎች በተግባር በመተርጎም ረገድ ያስመዘገበችው ውጤት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን እንደሚያረጋግጥ ገልጸዋል። ሀገሪቱ በዘርፉ የገነባችው አቅም ለአህጉሪቱ ትልቅ ማሳያ መሆኑንም አብራርተዋል።
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የኢጋድ አባል ሀገራት የኢትዮጵያን ተሞክሮ በመቅሰም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በየሀገራቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ውስጥ ማቀናጀት የሚያስችል አህጉራዊ አጋርነት መፍጠር መሆኑም ተመላክቷል። የአባል ሀገራቱ ተወካዮችም የኢትዮጵያን ልምድ በመቅሰም በጋራ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ እያከናወናቸው ያሉ የምርምር እና ልማት ስራዎችን
አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል። አያይዘውም ኢትዮጵያ ይህንን የቴክኖሎጂ እውቀትና ተሞክሮ ለሁሉም የኢጋድ አባል ሀገራት ለማካፈል እና በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። ይህ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የዲጂታል ትስስርን ለማጠናከር እና የቴክኖሎጂ አቅምን በጋራ
ለመጠቀም ሰፊ በር የሚከፍት መሆኑ ተገልጿል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute