ጎግል አማርኛና አፋን ኦሮሞን ጨምሮ 13 የአፍሪካ ቋንቋዎችን ያካተቱ አዳዲስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ፡፡
· AI Solutions
Google has introduced new AI-powered search features supporting 13 African languages, expanding access to artificial intelligence for millions of users across the continent.
ጎግል አፍሪካውያን በቋንቋቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን መጠቀም እንዲችሉ የሚያስችሉ አዳዲስ አገልግሎቶችን በ13 የአፍሪካ ቋንቋዎች መጀመሩን አስታወቀ።
ኩባንያው ይፋ ያደረጋቸው "AI Overviews" እና "AI Mode" የተሰኙት አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ጥገኝነት ወጥተው በማንኛውም መስክ መረጃን እንዲፈልጉ፣ እንዲማሩ እና የፈጠራ ስራዎችን እንዲያከናውኑ ታስበው የቀረቡ ናቸው።
ይህ ስራ ጎግል የአፍሪካ ቋንቋዎችን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ለማሳደግ ከሚሰራበት "Waxal" ከተሰኘው የምርምር ፕሮጀክት የተገኘ ውጤት መሆኑ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ የማሽን ለርኒግ እና የማህበረሰብ ተሳትፎን በማቀናጀት የቋንቋዎቹን ይዘት እና አካባቢያዊ አውድ ኤ.አይ እንዲረዳው ያስችላል።
በዚህ ዙር ከተካተቱ ቋንቋዎች መካከል አማርኛ እና አፋን ኦሮሞ የሚገኙበት ሲሆን በተጨማሪም ሶማሊኛ፣ ኪስዋሂሊ፣ ሀውሳ፣ ዮሩባ፣ ኢሲዙሉ እና አፍሪካንስን ጨምሮ 13 ቋንቋዎች ይገኙበታል።
ቴክ አፍሪካን ኒውስ እንደዘገበው ጎግል ይህንን እርምጃ መውሰዱ በአህጉሪቱ የሚገኙ ማህበረሰቦች ቴክኖሎጂውን ለትምህርት፣ ለንግድ እና ለፈጠራ ስራዎች እንዲጠቀሙበት ከማስቻሉም በላይ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን ፍትሃዊ እና ሁሉንም አሳታፊ ለማድረግ ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሏል።
ይህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አገልግሎት በአንድሮይድ እና በአይ.ኦ.ኤስ ስልኮች ላይ በሚገኘው የጎግል መተግበሪያ አማካኝነት ለተጠቃሚዎች ክፍት ሆኗል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute