“ኢንስቲትዩቱ የኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን ሽግግር የተግባር ማሳያ ነው ፡፡” የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች
· Other
nationwide “Tomorrow’s Day” program visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to observe its AI research, technological innovations, and efforts to develop solutions for Ethiopia and Africa.
ጳጉሜን 5 በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው"የነገ ቀን" መሰናዶ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የመንግስት መስሪያ ቤት፣ የሲቨክ ማህበራት እንዲሁም የስታርታፕ ተወካዮች
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩቱን የስራ እንቅስቃሴዎች በአካል በመገኘት ተመልክተዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ ባሻገር አፍሪካዊ ችግሮችን በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ታግዞ ለመፍታት በማከናወን ላይ የሚገኘውን የምርምር እና ልማት ስራዎችን በተመለከተ ለተቋማቱ ተወካዮች ዝርዝር ማብራሪያ ቀርቧል።
ጉብኝቱን አስመልክቶ ሀሳባቸውን ያጋሩ የልዑካን ቡድኑ አባላት ኢንስቲትዩቱ የኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን ሽግግር የተግባር ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የተሰሩ ስራዎች በማድነቅ ከሌሎች ዘርፎች እና ተቋማት ጋር በይበልጥ በትብብር መስራት ብሩህ ተስፋ ያላት የነገዋን ኢትዮጵያ እዉን ለማድረግ ጊዜዉ ያጠረ እንደሚሆን አንስተዋል። ልዑካኑ በነገዋ ኢትዮጵያ ግንባታ ላይ የመሪነት ድርሻ የወሰዱ መሰል የቴክኖሎጂ እና ልህቀት ማዕከላትን ተዘዋውረው በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute