ጂ.ፒ.ዩ
· AI Study
Modern Graphics Processing Unit technology has become a key driver of artificial intelligence, enabling faster data processing and powering advanced applications from autonomous vehicles to scientific research.
ግራፊክስ ፕሮሰሲንግ ዩኒት (GPU) በአንድ ጊዜ ብዙ ተግባራትን ለማከናወን የተነደፈ ከፍተኛ አፈጻጸም ያለው የኮምፒውተር ፕሮሰሰር ነው።
ለቪዲዮ ጨዋታዎች እና ምስሎችን ለማጫዎት ታስቦ የተሰራ ቢሆንም አሁን የኤ.አይ ሞዴሎችን ለማሰልጠን፣ ግዙፍ ዳታን ለመተንተን እንዲሁም ከፍተኛ አፈጻጸም ያላቸዉ ኮምፒውተሮችን ለማንቀሳቀስ ተመራጭ ነዉ። እነዚህን ተግባራት በሴንትራል ፕሮሰሲንግ ዩኒት (CPU) ማከናወን ቢፈለግ ካለዉ የአቅም ዉስንነት የተነሳ ቀናት አልያም ወራት ሊፈጅበት ይችላል።
ሹፌር አልባ ተሽከርካሪዎች፣ ቻት ቦቶች፣ የአየር ሁኔታ ትንበያ እና ሳይንሳዊ ምርምሮች ባሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ውስጥ ጂ.ፒ.ዩወሳኝ ሚና ይጫወታል። እንደ NVIDIA RTX 4090፣ NVIDIA A100 እና AMD Radeon RX 7900 XTX ያሉት ጂ.ፒ.ዩዎች ለቪዲዮ ጌም፣ ለኤ.አይ ቴክኖሎጂ ልማት እዲሁም ምርምር ተመራጭ ናቸዉ።
ጂፒዩ ኮምፒዩቲንግ ዘመናዊ የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ዉጤታማ የሚያደርግ ኃይል ሆኖ እያገለገለ መሆኑን የአይ.ቢ.ኤም ድረ ገጽ መረጃ ያሳያል። ኤንቪዲያ፣ኤ.ኤም.ዲ እና ኢንቴል ጂ.ፒ.ዩ በማምረት ፈር ቀዳጅ ከሆኑ ኩባንያዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute