ጉግል የአፍሪካ ቋንቋዎችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለማሳደግ ያለመ አዲስ የድምፅ መረጃ ስብስብ ይፋ አደረገ፡፡
· AI Study
Google and African researchers launch open-access WAXAL dataset to expand AI voice technology in 21 African languages.
ጉግልከአፍሪካ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር “ WAXAL” የተሰኘ የንግግር ዳታሴት ይፋ ማድረጉን አስታወቀ። ይህ ዳታሴትእንደ ስዋሂሊ፣ ሃውሳ፣ ዮሩባ እና ሉጋንዳን የመሳሰሉ ከሰሃራበታች የሚነገሩ 21 የአፍሪካ ቋንቋዎችን ያካተተነው።
የመረጃ ስብስቡ ዋነኛዓላማም ከዚህ ቀደም ጥራትያለው የተጠናቀረ የድምጽ የቋንቋ ግብዓት ባለመኖሩ ምክንያት በስልኮች ላይ የሚገኙ ምናባዊ ረዳቶችን ከመሰሉ የድምፅቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ መሆን ያልቻሉከ100 ሚሊዮን በላይ ተናጋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግና የዲጂታል ክፍተቱን መሙላት ነው።
ይህበጉግል የገንዘብ ድጋፍ ለሦስት ዓመታት የተከናወነ ፕሮጀክት 1,250 ሰዓታት የሚፈጅ የተፈጥሮ ንግግር እና የስቱዲዮቀረጻዎችን ይዟል።
መረጃ የማሰባሰቡን ስራ በግንባር ቀደምትነት የመሩት የተለያዩ የአፍሪካ የምርምር ተቋማት በመሆናቸው የመረጃው ባለቤትነትም በእነዚህ ተቋማት እጅ እንዲቆይ ተደርጓል። ይህም አፍሪካውያንተመራማሪዎችና ተማሪዎች በውጭ ኩባንያዎች ላይ ጥገኛሳይሆኑ በራሳቸው ቋንቋ እንዲሁም አካባቢያዊ ዐውድ የራሳቸውን የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች እንዲያበለጽጉ ያስችላቸዋል።
ኤ.አይ አፍሪካ በድረገፁ እንዳስነበበው በአሁኑ ወቅት ይህየ WAXAL ዳታሴት ለማንኛውም ተመራማሪ እና ስራ ፈጣሪበነጻ የቀረበ ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute