የጌትስ ፋውንዴሽን ኢትዮጵያ የጤናውን ዘርፍ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ለማዘመን የምታካሄደውን የምርምርና ልማት ሥራ አደነቀ።
· Other
Chris Elias, President of Global Development at the Gates Foundation, visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to learn about Ethiopia’s AI-driven health solutions and discuss stronger cooperation in research, development, and technology transfer.
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለጤናው ዘርፍ መሻሻል እየወሰደችው ያለው እርምጃ ዓለም አቀፍ አድናቆትን እያተረፈ ነው። የጌትስ ፋውንዴሽን የዓለም አቀፍ ልማት ፕሬዚዳንት ክሪስ ኤልያስ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን በመጎብኘት የሀገሪቱን የፈጠራ ስራዎች አድንቀዋል።
ጉብኝቱ ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ እያስመዘገበችው ያለውን ድልና የራስ አቅም ያሳየ ነው፡፡ጉብኝቱን ተከትሎ በተካሄደ ውይይት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ለጌትስ ፋውንዴሽን ልዑክ በሰጡት ማብራሪያ የጤናውን ዘርፍ አገልግሎት ለማሻሻል እየተተገበሩ የሚገኙ የኤአይ መፍትሄዎችን
አስረድተዋል። ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የኢንስቲትዩቱንቁርጠኝነት ገልጸው፤ የቴክኖሎጂ ሽግግሩ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ከጌትስ ፋውንዴሽን ጋር የሚደረገው ትብብር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
የጌትስ ፋውንዴሽን የዓለም አቀፍ ልማት ፕሬዚዳንት ክሪስ ኤልያስ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በራስ አቅም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ እያደረገችመሆኑን አድንቀዋል። ኤአይ የጤናውን ዘርፍ ለማሻሻል ያለውን ከፍተኛ ሚና በማንሳት፤ከኢንስቲትዩቱ ጋር በምርምር እና ልማት የሚደረገው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ይህ በጤናው ዘርፍ የሚደረገው የቴክኖሎጂ ሽግግር የዕለት ተዕለት አገልግሎትን ከማሻሻል ባለፈ የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት የሚያረጋግጥ እና በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት ከፍ የሚያደርግ ቁልፍ እርምጃ ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute