በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር በኢንስቲትዩቱ የስራ ጉብኝት አካሄዱ።
· Visiting
Finnish Ambassador Visits EAII and Pledges Support for Ethiopia’s Growing AI Ecosystem
በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ኤሪክ ሉንድበርግ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተገኝቶ የስራ ጉብኝት አድርጓል።
የኢንስቲትዩቱ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊና የቴክኖሎጂ አማካሪ ሻምበል ይልማ (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ የኤ.አይ (AI) ቴክኖሎጂ ሥነ-ምህዳርን ምቹ ከማድረግ እና በዘርፉ ችግር ፈቺ ምርምሮችን ከማከናወን አንጻር እየሰራቸው ስላሉ ተግባራት ለልዑካኑ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አምባሳደር ኤሪክ ሉንድበርግ በበኩላቸው በኢንስቲትዩቱ እየተከናወኑ የሚገኙ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ልማት ስራዎች እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አያይዘውም ፊንላንድ በዘርፉ ያላትን የዳበረ ልምድ በማካፈል በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute