ፍትሕን በቴክኖሎጂ ለማዘመን
· Visiting
Oromia Supreme Court and EAII Strengthen Partnership to Advance Smart Court Solutions
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍቤት ፕሬዝዳንት የተከበሩ ኡቱካና ኦዳ (ዶ/ር) የተመራ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ የፍትሕ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የተጀመሩ
ስራዎችን በቅርበት ለመመልከት በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ ጉብኝት አድርጓል።
ልዑካኑን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ተቀብለው አነጋግረዋል። በውይይቱም በሁለቱ ተቋማት መካከል እየተከናወኑ ያሉ
የቴክኖሎጂ ልማት ስራዎች የተገመገሙ ሲሆን፤ ለወደፊት ትብብሩን የሚያጠናክሩ የአሰራር ማዕቀፎችን በተመለከተም አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
ኢንስቲትዩቱ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የአሰራር ስርዓቶችን የሚያዘምኑ የስማርት ፍ/ቤት እና ተያያዥ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን ሲያበለጽግ ቆይቷል።
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስም የፍትሕ ስርዓቱን ተደራሽነት፣ ተጠያቂነትና ውጤታማነት በማሳደግ ረገድ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።
የተከበሩ ኡቱካና ኦዳ (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ እያከናወናቸው ያሉት የምርምርና ልማት ስራዎች የሚያስደንቁ መሆናቸውን ገልጸዋል። የሁለቱን ተቋማት ሁለንተናዊ
ትብብር ይበልጥ ለማጠናከርም ፍቤቱ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። ልዑካኑ የኢንስቲትዩቱን የሮቦቲክስ ወርክሾፕ፣ የምርት ማሳያ
ክፍሎችና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute