አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለአፍሪካ አንድ ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ተጨማሪ የሃብት አማራጭ ይዞ እየመጣ መሆኑ ተገለፀ፡፡
· AI Investment
A new AfDB report outlines how artificial intelligence can drive productivity, inclusive growth, and economic transformation across Africa, with major gains expected in agriculture, industry, finance, and health.
በአፍሪካ ልማት ባንክ የወጣ አዲስ ሪፖርት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በ2035(እ.ኤ.አ) በአፍሪካ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ላይ እስከ 1 ትሪሊዮን ዶላር ሃብት ሊጨምር እንደሚችል ተጠቆመ፡፡ ይህም የአህጉሪቱን አሁናዊ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ምርት አንድ ሦስተኛውን ያህል ነው።
ይህ ዕድል ሊገኝ የሚችለው አፍሪካ እያደገ ባለው የዲጂታል አቅሟ፣ በወጣት የሰው ኃይል ብዛቷ እና እየተከናወኑ ባሉ ዘርፈ-ብዙ ማሻሻያዎች ምክንያት ነው፡፡ ይህም አህጉሪቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለኤ.አይ ዕድገት ተመራጭ ከሆኑ አካባቢዎች አንዷ ያደርጋታል።
እንደ ሪፖርቱ መረጃ ይህ ከኤ.አይ የሚገኝ ሃብት ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ አምስት ዘርፎች እንደሚገኝ የተጠቆመ ሲሆን ዘርፎቹ በጥቅሉ ከቴክኖሎጂው የሚገኘውን ትርፍ 58 በመቶ ወይም 580 ቢሊዮን ዶላር ያህሉን ድርሻ ይይዛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዘርፎቹም ግብርና፣ የጅምላ ሽያጭ እና የችርቻሮ ንግድ፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ኢንዱስትሪ 4.0፣ ፋይናንስ፣ የጤና እና የሕይወት ሳይንስ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ይህንን ዕድል ዕውን ለማድረግ አምስት ቁልፍ ጉዳዮች እንደ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጠዋል፡፡ እንዚህም መረጃ፣ የኮምፒውተር መሠረተ ልማት፣ የመስኩ ክህሎቶች፣ አስተዳደራዊ ተዓማኒነት እና የካፒታል ተደራሽነት ናቸው።
የአፍሪካ ልማት ባንክ በእነዚህ ዘርፎች ኢንቨስትመንቶችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን በድረ ገጹ ባወጣው መረጃ ያመላከተ ሲሆን መንግስታት እና የግሉ ዘርፍ ስትራቴጂውን ወደ ተግባር ለመተርጎም በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute