የተማሪዎችን የኤ.አይ ክህሎት ለማሳደግ በማለም ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
· Education
EAII Expands AI Clubs in Dire Dawa to Build Future Talent, Digital Skills, and Innovation Capacity.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ላቋቋማቸው ሁለት የኤ.አይ ክበብ አባላት ለሦስት ቀናት ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች ከሳቢያን እና ከድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች ናቸው። ስልጠናው ተማሪዎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት እውቀትን ከንድፈ-ሀሳብ ባለፈ በተግባር እንዲለማመዱ ለማስቻል መሰረታዊ የኤ.አይ ክህሎት፣ ማሽን ለርኒንግ፣ ዲፕ ለርኒንግ እና ጄነሬቲቭ ኤ.አይ ላይ ያተኮሩ ማብራሪያዎችንና ልምምዶችን አካቷል።
ኢንስቲትዩቱ ታዳጊዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰጣቸው እነዚህ ስልጠናዎች፥ ለሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ልማት የጀርባ አጥንት የሚሆን እና በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ መሆን የሚችል ብቁ የሰው ኃይል በረጅም ጊዜ ለማፍራት ጽኑ መሠረት የሚጥሉ ናቸው።
ኢንስቲትዩቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኤ.አይ ክበባትን የማደራጀትና ተግባራዊ ስልጠናዎችን ለታዳጊዎች ተደራሽ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute