45ተኛዉ ጂ.አይ.ቴክስ ግሎባል 2025 (GITEX GLOBAL) ኤክስፖ ተጠናቀቀ፡፡
· Visiting
GITEX GLOBAL 2025 Concludes in Dubai, Showcasing AI Innovations and Strengthening Global Partnerships — Ethiopia’s EAII Delegation Explores Collaborative Opportunities.
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ180 ሀገራት የተውጣጡ ተወካዮች የተሳተፉበት ጂ.አይ.ቴክስ ግሎባል 2025 (GITEX GLOBAL) ተጠናቋል።
45ተኛዉ ጂ.አይ.ቴክስ ግሎባል 2025 የኤ.አይ ቴክኖሎጂን የተላበሱ አዳዲስ ፈጠራዎች የተዋወቁበት እና፣ የዘርፉ አንቀሳቃሾች ያካበቱትን ልምድ ያጋሩበት መድረክ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ሥነ-ምግባራዊ ትግበራና ቁጥጥርን የተመለከቱ ዉይይቶች በሰፊው ሽፋን ያገኙበት ሁነት ሆኖ አልፏል።
“Powering the Future through AI & Tech” በሚል መሪ ቃል በዱባይ በተካሄደው ሁነት ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑካን ቡድን ተሳትፏል። በዚህም በሁነቱ ዓለም በመስኩ የደረሰበትን ደረጃ ለመገንዘብ ከማስቻሉማ በሻገር ለተቋሙ ዓለማቀፍ ትስስሮችን መፍጠር የሚያስችሉ ውይይቶች ተደርገውበታል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute