የአፍሪካ ሀገራት መከላከያ ሚኒስትሮች፣ ወታደራዊ አታሼዎች፣ አምባሳደሮች፣ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት ተጋባዥ እንግዶች ኢንስቲትዩቱን ጎበኙ።
· Visiting
High-level African and UN delegation visits EAII, affirming commitment to digital sovereignty and innovation leadership.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ጎብኝዎቹን ተቀብዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የኢንስቲትዩቱን የስራ እንቅስቃሴዎች በተመለከተ ለጎብኚዎቹ ገለፃ አድርገውላቸዋል። ኢንስቲትዩቱ ኤ.አይን ለተለያዩ ዘርፎች የችግር መፍቻ ቁልፍ አድርጎ ሲስተሞችና መተግበሪያዎችን እያለማ መሆኑ በምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተብራርቷል፡፡
ጎብኚዎቹ ባዩት ነገር መደነቃቸውን ገልፀው ኢንስቲትዩቱ የሚሰራቸው ስራዎች ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም አርዓያ መሆን የሚችሉ ናቸው ብለዋል፡፡ በተለይ በስታርትአፕ ማዕከል የሚሰሩ ሰራዎች ከኢትዮጵያ አልፈው ለአፍሪካም ኩራት መሆን የሚችሉ ወጣቶችን ለመፍጠር እንደሚያስችል አብራርተዋል።
ጎብኚዎቹ የኢንስቲትዩቱን ስታርትአፕ ማዕከል፣ የሮቦቲክስ ወርክ ሾፕ፣ ዳታ ሴንተር እና የምርት ማሳያ ክፍልን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute