የማሌዥያ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምርመራዎችን ለማጠናከር የኤ.አይ ቴክኖሎጂን እየተጠቀመ ነዉ።
· AI Solutions
Malaysia and Ethiopia Harness Artificial Intelligence to Detect Corruption Risks, Analyze Financial Patterns, and Strengthen Investigations
የማሌዥያ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የኤ.አይ ቴክኖሎጂን እየተጠቀመ ነዉ። ኤአይን የመጠቀም ዉሳኔው ዉስብስብና ለመለየት አስቸጋሪ የሆኑ የሙስና ጉዳዮችን ቀድሞ ለመለየት እንዲሁም የሙስና አደጋዎች ከመከሰታቸዉ በፊት ለመለየት ያለመ ነዉ።
በዚህም የኤ.አይ ቴክኖሎጂ የመረጃ ትንተናዎች በፍጥነት እንዲከወኑ ብሎም በሚገኘዉ ዉጤት የሚወሰደዉ እርምጃ ዉጤታማ እንደሚሆን ታምኖበታል። በዚህም ከፍተኛ መጠን ያላቸውን መረጃዎች ለመተንተን ኤአይን መጠቀም በኮሚሽኑ ተመራጭ ሆኗል። ያልተለመዱ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን ለመለየት፣ የገንዘብ ፍሰቶችን ለመከታተል እንዲሁም በግለሰቦችና በኩባንያዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ለመለየት የኤ.አይ ቴክኖሎጂን አቅም ጠቀሜታ ጉልህ ሆኗል።
ኢትዮጵያም በኢንስቲትዩታችን የብሔራዊ የሙስና ወንጀል ጥቆማ መስጫ ስርዓት (NCRS) አልምታ ከሁለት ዓመት በፊት ጥቅም ላይ በማዋል ዜጎችና መንግሥት በጋራ የፀረ ሙስና ትግሉን እያካሄዱ መሆኑ ይታወቃል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute