የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በጋራ ለመስራት ውይይት አካሄዱ፡፡
· Other
EAII and Gates Foundation Explore Partnership to Advance AI Innovation, Digital Transformation, and Sustainable Development
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ታዋቂው ዓለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በቴክኖሎጂ ልማትና ትግበራ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ ውይይት አከናውነዋል።
በፋውንዴሽኑ የአፍሪካና የህንድ ቢሮዎች ፕሬዝዳንት አንኩር ቮራ የተመራው ልዑካን ቡድን በኢንስቲትዩቱ የስራ ጉብኝት ያደረገ ሲሆን ጉብኝቱ በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ አዳዲስ የትብብር ምዕራፎችን ለመክፈት ያለመ ነው።
ከጉብኝቱ ጎን ለጎን በተደረገው ዉይይት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ሰው ሰራሽ አስተወሎት እንዴት ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተለይም በግብርና፣ በጤና፣ በፋይናንስ እና በትምህርት ዘርፎች የተሰሩ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለልዑካን ቡድኑ ቀርበዋል። ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚካሄደው ይህ የሁለትዮሽ ውይይት የክላውድ መሠረተ ልማት፣ የሰው ኃይል ልማትና የስታርታፕ ድጋፍ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ሀገሪቱ በዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ጉዞ ለማፋጠን የተቋቋመ የመንግስት የልህቀት ማዕከል ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2000 የተመሰረተው የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና እና በድህነት ቅነሳ ዙሪያ የሚሰራ ግዙፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute