የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራር እና ሰራተኞች ዓለማቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ።
· Other
Staff of the Ethiopian Artificial Intelligence Institute commemorated International Women’s Day, highlighting the importance of women’s participation and leadership in the rapidly growing field of artificial intelligence.
በዓለማቀፍ ደረጃ ለ115ኛ በሀገራችን ለ50ኛ ጊዜ “50 ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነት እና ለበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ያለውን ዓለማቀፍ የሴቶች ቀን የኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች በተገኙበት በተቋም ደረጃ ተከብሮ ውሏል።
ቀኑን በማስመልከት መልዕክት ያስተላለፉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ዕለቱን ከመዘከር ባለፈ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች በስፋት እየተሰራ ስለመሆኑም ተናግረዋል።ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው በተቋሙ የሚገኙ ሴቶችን በተለየ መንገድ ወደ አመራርነት የማሳደግ፣ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ የማስተማር እና የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ በማድረግ ሴቶችን የማብቃት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።
በመድረኩ በዓሉን የሚዘክር የፖናል ውይይት የተደረገ ሲሆን እለቱን የተመለከተ የጥያቄና መልስ ውድድር ተደርጓል። በተጨማሪም ከመከላከያ ሚኒስቴር የመጡ ሴት አመራሮች ተሞክሮአቸውን ለተሳታፊዎች አጋርተዋል።
የሴቶችን ቀን በየዓመቱ ከመዘከር ባለፈ የሴቶችን ተጠቃሚነት እና እኩልነት የሚያረጋግጡ ስራዎች በተግባር ሊታዩ እንደሚገባም በመድረኩ ተነስቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute