“የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አህጉራዊ የልህቀት ማዕከል ለመሆን የሚያስችሉ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን እያከናወነ ነው’’ አቶ ይታገሱ ደሳለኝ
· Visiting
EAII Showcases AI Innovations Driving Smart Policing, Digital Public Services, and National Transformation in Ethiopia
በፌደራል ፖሊስ የአስተዳደርናልማትጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ነብዩ ዳኜ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስኢንስቲትዩትን ጎበኘ፡፡
የኢንስቲትዩትምክትል ዋና ዳይሬክተርአቶይታገሱ ደሳለኝ ኢትዮጵያን በዓለም የቴክኖሎጂ መድረክ ተወዳዳሪ እና የአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን የሚያስችሉዘርፈ ብዙ ስራዎችን ኢንስቲትዩቱ በቁርጠኝነት እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩአክለውም ከተቋቋመ አጭር ጊዜ የሆነው ይህ ኢንስቲትዩትእንደመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ስማርት ሲቲ እና EFP Appን የመሳሰሉ ፕሮጀክቶችን መተግበር መቻሉን ጠቅሰው፤ በጤናው ዘርፍም የህክምና አገልግሎትአሰጣጥን የሚያሻሽሉ በርካታ ሲስተሞችንበማልማት ረገድ ስኬታማ ስራዎች እየተከናወኑመሆኑን አብራርተዋል።
የፌደራል ፖሊስ የልዑካን ቡድን አባላት በኢንስቲትዩቱ ሀገራዊ አበርክቷቸው ጉልህ የሆኑ ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑ መገንዘባቸውን ገልጸዋል። በተለይም ኢንስቲትዩቱ ለፌደራል ፖሊስ ያበለጸገው የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ወንጀል የመከላከል ስራውን በእጅጉ እያገዘ እንደሚገኝምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
በተጨማሪምበአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን “ስማርት ፖሊስ ስቴሽን” ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ያስታወሱት ጎብኝዎቹ፤ በከተማዋ እና በከልል ከተሞች በተገጠሙ ካሜራዎች አማካኝነት የወንጀል መከላከል ተግባራትን በላቀ ሁኔታ ማከናወን መቻሉንም አስታውቀዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute