አማዞን ስቱዲዮ የቴሌቪዥን እና የፊልም ፕሮዳክሽኑን ውጤታማነት ለማሳደግ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለመጠቀም አቅዷል፡፡
· AI Investment
Amazon integrates AI into film and TV production to cut costs and accelerate content creation for Prime Video.
እንደ ሮይተርስ ዘገባ አማዞን የሰውሰራሽ አስተውሎትን ቴክኖሎጂን በፊልም እናበቴሌቪዥን ዝግጅቶቹ በመጠቀም የፕሮግራሞቹን ጥራት ለማሳደግ እናወጪን ለመቀነስ አቅዶ እየሰራ ነው።
ይህ የአማዞን ስቱዲዮ ዕቅድ የይዘት ፈጠራን በማፋጠን በስርጭት ፉክክር ውስጥ የላቀ የተወዳዳሪነት ጥቅምን ያስገኛል።
በሂደቱም በቅድመ ፕሮዳክሽን በኤ.አይ የታገዘ የስክሪፕት ትንተና እናየታሪክ ቅደም ተከተልሰሌዳ ማመንጨት ያስችላል። በቀረጻ ወቅት ደግሞ ምናባዊ ስፍራዎችን በመፍጠር ረገድ ለቀረጻ የሚውሉ የቦታ ወጪዎችን ይቀንሳል። በድህረ-ፕሮዳክሽን ኤ.አይ የድምጽ እና የምስል አርትዖትን ያፋጥናል።
ሂደቱ እየናረ ያለውን የይዘቶች በጀት በመቆጣጠር ወጪ ቆጣቢ አማራጭ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute