የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
· Visiting
Dire Dawa City Mayor Leads Delegation Visit to EAII to Strengthen Smart City and Digital Ethiopia Collaboration
በድሬድዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሃር የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉበኝት አድርጓል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ስለኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ ገፅታ ለጎብኚዎቹ ገለፃ አድርገዋል። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ ለተለያዩ ዘርፎች ስላለማቸው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና በስታርታፕ ማዕከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል። በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር አብሮ ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው ወደፊትም ይህ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አመላክተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት ከጉብኝቱ በተጨማሪ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ በውይይቱ ላይ የድሬድዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሃር ኢንስቲትዩቱ ዲጅታል ኢትዮጵያን ዕውን በማድረግ ሂደት እየሰራ ያለው ስራ የሚያኮራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በስማርት ሲቲ ግንባታ እና በሌሎችም ዘርፎች ኢንስቲትዩቱ ለከተማ አስተዳደሩ የሰራቸውን ስራዎች በማውሳት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ከንቲባው በንግግራቸው ጉብኝቱ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ያየንበት እና ምቹ የስራ አካባቢን እንዴት መፍጠር እንደሚቻል የተማርንበት ነው ብለዋል፡፡
ጎብኚዎቹ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ኤ.አይ ለሀገር እድገት ያለውን አስተዋፆ በመረዳት የሚሰራቸው ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም የኢንስቲትዩቱን የስራ ባህልና የተቋም ግንባታ ትምህርት የሚወስዱበት እና የተሻለ አቅም የሚፈጥርላቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute