የዓለም ባንክ የጤና ቡድን ልዑካን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አካሄደ።
· Visiting
World Bank Health Team Explores AI Partnerships with EAII to Strengthen Ethiopia’s Health System
በኢትዮጵያ በኤ.አይ የታገዘ የጤና ሥርዓትን ከመዘርጋት አንጻር ትብብርን ለማጠናከር ያለመዉ ጉብኝቱ የዓለም ባንክ ጤና ቡድን እንዲሁም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ልዑካንን ያሳተፈ ነበር።
ልዑካኑ ኢንስቲትዩቱ በጤናዉ ዘርፍ የሰራቸዉን ስራዎች ተመልክተዋል። በተጨማሪም በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመለየት እና ለመቅረፍ የሚያግዝ ዉይይት ከኢንስቲትዩቱ አመራሮች ጋር ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ይህ ጉብኝት ፍትሐዊ የጤና ሥርዓት ለመዘርጋት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ብሎም ጥራትን ለማሻሻል የሚያስችል የረጅም ጊዜ አጋርነት ለመመስረት ወሳኝ እርምጃ ነዉ ብለዋል። ልዑካኑ ላደረጉት ጉብኝትም ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
በዓለም ባንክ የጤና ቡድን መሪ እና ከፍተኛ የጤና ስፔሻሊስት የሆኑት ፀጋነህ አምሳሉ ኢንስቲትዩቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ኢንቨስትመንቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ወሳኝ ከሆኑ ተቋማት መካከል አንዱ ነዉ ብለዋል። ኢንስቲትዩቱ በጤናዉ ዘርፍ የሰራዉ ስራ የሚደነቅ መሆኑም በጉብኝቱ ተገልጿል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute