የጋና ጦር ኃይሎች የአዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ አባላት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
· Visiting
College Delegation Praises Ethiopia’s AI Progress as a Driver of Continental Innovation, Global Competitiveness, and Digital Productivity
የኮሌጁ ልዑካን በኢንስቲትዩቱ በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ዘርፍ እያሳየች ያለው ለውጥ የአህጉሩ ፋና ወጊ እንደሚያደርጋት ገልጸዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ እያከናወነ ያለው ተግባር አስገራሚና ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን የተናገሩት ልዑካኑ፤ በኢንስቲትዩቱ የተመለከቱት የቴክኖሎጂ ዝግጁነትና የሥራ ሂደት የሚደነቅ እንደሆነ አብራርተዋል። ሀገሪቱ የጀመረችው የቴክኖሎጂ ሽግግር በዚሁ ፍጥነት ከቀጠለ በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ በዓለማቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቷን እንደምታረጋግጥ ያላቸውን እምነት ጠቁመዋል።
ለጎብኚዎቹ ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ዘርፎች የሚያከናውናቸውን ተግባራት በተመለከተ በአመራሮች ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ በገለፃው ተቋሙ ኤ.አይን በተገቢው መንገድ ለመምራት እንዲያስችለው ብሔራዊ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ በማዘጋጀት እና በማፀደቅ ወደ ስራ ማስገባቱ ተመላክቷል፡፡
ልዑካኑ በቆይታቸው በኢንስቲትዩቱ ውስጥ የሚከናወኑ የቴክኖሎጂ ምርምሮችን፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን እና የሥራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው
ተመልክተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute