ማይክሮሶፍት ለሰው ልጅ ደህንነትና ክብር ቅድሚያ የሚሰጥ አዲስ የኤ.አይ የሥነ-ምግባር መመሪያ ሊያወጣ ነው።
· Other
Microsoft Introduces Draft Ethics Guidelines to Ensure Future AI Models Remain Understandable, Correctable, and Under Human Control
ማይክሮሶፍትበቀጣይ የሚያበለጽጋቸውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴሎች ምርምር እና ልማት በትክክለኛው አቅጣጫ ለመምራት የሚያስችል አዲስ የሥነ-ምግባር ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
በረቂቅ መመሪያው መሠረት የማይክሮሶፍት የኤ.አይ ሥርዓቶች ከሰዎች የሚሰጣቸውን ማስተካከያዎች መቀበል፣ ለሰዎች ሊገባ በሚችል መንገድ መግባባት እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተግባራቸው በሰዎች ቁጥጥር ሥር መሆን የሚችሉበትን አቅጣጫ ማካተት ዋና ትኩረቱ ነው።
ኩባንያው ይህንን መመሪያ ለማዘጋጀት የዘርፉ ባለሙያዎችን ያሳተፈ የብዙ ወራት የጥናት እና የውይይት ጊዜያት እንደወሰደ ገልጿል። የሕዝብ አስተያየትንም የሚያካትተው መመሪያ ኩባንያው በቀጣይ የሚያበለጽጋቸውን የኤ.አይ ሞዴሎች ለማሠልጠን እንደ መሠረታዊ አቅጣጫ ይውላል።
የማይክሮሶፍት ኤ.አይ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙስጠፋ ሱሌይማን መመሪያው ኩባንያው ለሚያለማቸው የኤ.አይ ሥርዓቶች ሁሉ መሰረት እንደሚሆን ተናግረዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute