የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራር እና ሰራተኞች የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሄዱ
· Other
The Ethiopian Artificial Intelligence Institute conducted its 2018 E.C. tree-planting program in Bishoftu, supporting Ethiopia’s national Green Legacy initiative under the theme “Planting Hope.”
የኢትዮጵያ አርቲፊሻልኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዘንድሮ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለውን የአረንጓዴ ዐሻራ ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል የ2018 ዓ.ም የችግኝተከላ መርሃ-ግብሩን በቢሾፍቱ ከተማ አከናውኗል።
በመርሃ-ግብሩላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የችግኝ ተከላ ስራ ከስነ-ምህዳር ጥበቃ ባለፈ የወደፊቷን ኢትዮጵያ የልማትና የብልጽግና መሰረት የሚጥል፣ ለትውልድ የሚሸጋገር ታላቅ ኃላፊነትነው ብለዋል። አክለውም ኢንስቲትዩቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ከሚጫወተውየመሪነት ሚና ባሻገር የሀገሪቱን ታላቅ የለውጥ ጉዞ በሚደግፉ የግብርና፣ የማህበራዊናየልማት እንቅስቃሴዎች ላይ በግንባር ቀደምትነት የመሳተፍ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትርዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ ሀገራችን ኢትዮጵያ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪቃል በዘንድሮው ዓመት ብቻ 8 ቢሊየን ችግኞችን ትለብሳለች።ይህም ቀደም ሲል ከተከናወኑት አረንጓዴ ዐሻራዎችጋር ሲደመር የችግኞቹን ቁጥር ወደ 56 ቢሊየን ያደርሰዋል፡፡ በቀጣይየምታዘጋጀውን ታላቁን የዓለማቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) ምክንያት በማድረግ አጠቃላይ የተተከሉ ችግኞችን ወደ 65 ቢሊየን ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው። ጠቅላይሚኒስትሩም ይህ ሀገራዊና ቀጠናዊ ራዕይ እንዲሳካ ሁሉም ዜጋ በአንድነትና በባለቤትነት ስሜት እንዲነሳ ጥሪ አቅርበዋል።
በዕለቱ የተሳተፉትየኢንስቲትዩቱ አመራር እና ሰራተኞችበበኩላቸው፤ የአረንጓዴ ዐሻራመርሃ-ግብር የሀገራችንን የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጥና የኢኮኖሚ ህዳሴያችንን የሚያፋጥን በመሆኑ ህዝባዊ ጥሪውን መመለስ የዜግነት ግዴታችን ነው ብለዋል። በተጨማሪም በጥቂት ቀናት ውስጥ ለሚካሄደውና የታላቅነታችን ማሳያ ለሆነው የአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ታሪክ እንዲሰራ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በዘንድሮው የኢንስቲትዩቱ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር የተተከሉት ችግኞች ልክ እንደ ባለፉት ስድስት ተከታታይ ዓመታት ሁሉ የአፈር መሸርሸርን ከመከላከል ባሻገር፤ ለምግብነት የሚውሉና ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ዘላቂ ፋይዳ ያላቸው ናቸው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute