የሶማሊያ ልዑካን ቡድን አባላት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
· Visiting
Somalia and Ethiopia Explore Regional Partnership to Advance Artificial Intelligence
በሶማሊያ አርቲፊሻል ኢንተለንጀስ ኢንስቲትዩት ዋና ኃላፊ አብዲ ካቬን ሞሃዲን (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መሥሪያ ቤትን ጎብኝቷል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘዉዴ ለጎብኚዎቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በጤና፣ በግብርና፣ በሕግ ማስከበር፣ በፍትሕ ዘርፍ እና ሃገራዊ ቋንቋዎችን የማሽን መገልገያ ቋንቋ በማድረግ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ አቶ ተስፋዬ ለልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል፡፡
በምርምር፣ በተፈጥሮ ቋንቋ ቅንብር እና በሮቦቲክስ መስክ የተከናውኑ ተግባራትን፣ በዘመናዊ የኤ.አይ ቴክኖሎጂዎች የተደራጀዉን ሾዉ ሩም እንዲሁም የኢመርሲቭ ቴክኖሎጂን ልዑካኑ ጎብኝተዋል፡፡
ልዑካኑ ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት በኢንስቲትዩቱ በተመለከቱት ነገር መደሰታቸዉን ተናግረዋል፡፡ በጋራ ለመስራትም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸዉ ነዉ ያረጋገጡት፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute