የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የኢፍጣር መርሓ ግብር አካሄደ፡፡
· Other
The Ethiopian Artificial Intelligence Institute hosted a Ramadan Iftar gathering attended by Temesgen Tiruneh and religious leaders, fostering unity, dialogue, and shared values during the holy month.
በመርሓ ግብሩ ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ም/ጠቅላይ ሚንስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎቸ፣ የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን በመርሓ ግብሩ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው የተለያዩ አካላትን በአንድ ላይ በማሰባሰብ እና በህብረት የኢፍጣር መርሃግብር በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ላደረገው ለኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
መርሓ ግብሩ በተለያዩ የስራ ክፍሎች የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች በአንድ ላይ እንዲገናኙ እና የጋራ ቤተሰባዊ መንፈስ እንዲፈጥሩ ከማስቻል ባለፈ በረመዳን ወር የሚታየውን የመረዳዳት፣ የመተሳሰብ እና ተካፍሎ የመብላት እሴቶችን መሰረት ያደረገ ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute