የሕዝብ አገልግሎቶችን ለማሻሻል በሜታ የሚደገፍ የኤ.አይ ቡድን በዩናይትድ ኪንግደም ተቋቋመ፡፡
· AI Solutions
According to Reuters, the UK government has established a Meta-supported artificial intelligence team to develop open-source AI systems aimed at improving transportation planning, public safety operations, and national security decision-making.
የብሪታንያ መንግሥት የመጓጓዣ፣ የሕዝብ ደህንነት እና የመከላከያ አገልግሎቶችን ለማሻሻል የሚያስችሉ የኤ.አይ ስርዓቶችን ለመገንባት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ለዚህም ከሜታ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የኤ.አይ ባለሙያዎች ቡድን ማቋቋሙን ሮይተርስ አስነብቧል፡፡
የሀገሪቱ መንግሥት የስራ ምርታማነትን ለማሻሻል የኤ.አይ ቴክኖሎጂን መጠቀም እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡
የኤ.አይ ባለሙያዎቹ ባለስልጣናት ለቀጣዩ ዓመት የመንገዶች ጥገናን የሚከውኑበት፣ የሕዝብ ደህንነትን የሚያስተዳድሩበት እና በብሔራዊ ደህንነት ላይ ውሳኔዎችን ለማሻሻል የሚያስችሉ ኦፕን ሶርስ የኤ.አይ መሳሪያዎችን የሚያዘጋጁ ይሆናል፡፡
ቡድኑ ከአላን ቲዩሪንግ ኢንስቲትዩት የተውጣጣ የዳታ ሳይንቲስት እና የዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችን ያካተተ ነው፡፡
ስርዓቶቹ በመንግሥት ባለቤትነት ስር እንደሚሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ሚስጥራዊ መረጃዎችን በራሳቸው እንዲይዙ እና ቴክኖሎጂውን እንደ አስፈላጊነቱ እንዲያስተካክሉ ያስችላቸዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute