ቻይና የዓለማችንን ፈጣን ሱፐርኮምፒውተር ዘውድ ከአሜሪካ ነጠቀች
· AI Solutions
China Tops Global Supercomputer Rankings, Strengthening Digital Sovereignty and Leadership in AI and High-Performance Computing.
ቻይና አሜሪካን በመብለጥ በዓለም ፈጣን ሱፐር ኮምፒውተሮች ደረጃ አንደኛ መሆኗን ይፋዊው የTOP500 ዝርዝር አስታወቀ።
በጀርመን ይፋ በተደረገው በዓመት ሁለት ጊዜ በሚወጣው ደረጃ መሠረት በሸንዘን ብሔራዊ የሱፐር ኮምፒውተር ማዕከል የሚገኘው ላይንሻይን የተባለው
የቻይና ሱፐር ኮምፒውተር እስካሁን መሪ የነበረውን የአሜሪካው ኤል ካፒታን 20 በመቶ በመብለጥ በምድር ላይ እጅግ ኃያሉ ሥርዓት ሆኗል። ይህም እ.ኤ.አ ከ2017 ወዲህ አንድ የቻይና ኮምፒውተር የዓለምን መሪነት ሲረከብ የመጀመሪያው ነው።
በTOP500 ደረጃ መሰረት አሜሪካ በኤል ካፒታን፣ በፍሮንቲየር እና በአውሮራ ከ2 እስከ 4 ደረጃዎችን የያዘች ሲሆን ጀርመን በጁፒተር ሱፐርኮ ምፒውተር 5ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
በከፍተኛ 20 ውስጥ ከተካተቱ ሌሎች አገሮች ውስጥ እንግሊዝ፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጣሊያን፣ ኔዘርላንድስ እና ስዊዘርላንድ ይገኙበታል።
እንደ አልጀዚራ ዘገባ ይህ የቻይና ስኬት በዓለማቀፍ የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የሳይንስ የበላይነት ፉክክር ላይ ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥራል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute