የብሔራዊ ባንክ ገዥ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
· Visiting
Eyob Tekalign, Governor of the National Bank of Ethiopia, visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to observe its technological innovations and ongoing AI initiatives.
የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በኢንስቲትዩቱ ጉብኝት አካሂደዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ስለኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ስራዎች እና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡
የባንኩ ገዥ በኢንስቲትዩቱ ባዩት የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና ኢንስቲትዩቱ ራዕዩን ለማሳካት እየሰራ በሚገኘው ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የብሄራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በኢንስቲትዩቱ የሚገኙ የምርት ማሳያ ክፍል፣ የሮቦቲክስ ወርክሾፕ፣ የኤ.አይ ስታርታፕ እና ኤ.አይ ዩኒፖድን ተዘዋወረው ተመልክተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute