የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዝግጁነት ምዘና ፕሮጀክት ማስጀመሪያ እና የባለድርሻ አካላት ምክክር ተካሄደ።
· Other
“Ethiopia and UNESCO Unite to Advance Ethical AI Governance Through a Data-Driven National Readiness Assessment”
በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዝግጁነት ምዘና ፕሮጀክት ላይ በዛሬው ዕለትምክክር ተካሂዷል። መድረኩ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና በዩኔስኮ በጋራ የተዘጋጀ ነው።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታዬ ግርማ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያን የኤ.አይ ሥነ-ምህዳር አሁናዊ ገጽታን በመረጃ በተደገፈ ትንተና ለማቅረብ፣ ተቋማዊ እና የቁጥጥር ክፍተቶችን ለመለየትና ለሀገሪቱ ሁኔታ ተስማሚ የሆኑ ተግባራዊ ምክረ ሀሳቦችን ለማቅረብ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።
በመድረኩ ላይ በተደረጉ ገለጻዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በተካሄዱ ውይይቶች ፤ ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት አስፈላጊነትን፣ የቁጥጥር ደንቦችን ማጠናከርና ከፍተኛ አፈጻጸም ያላቸውን የኮምፒዩቲንግ መሠረተ ልማት ክፍተቶችን መፍታት እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።
ፕሮጀክቱ በመንግስት፣ በአካዳሚክ ተቋማት እና በግሉ ዘርፍ መካከል የባለድርሻ አካላት ውይይት ያካተተ ሲሆን ጠንካራና በመረጃ የተደገፉ ምክረ ሀሳቦችን ለማምጣት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህም የብሔራዊ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስትራቴጂው ከዓለማቀፍ አሰራሮች ጋር የተጣጣመ መሆኑን እና ኤ.አይ ለአካታች እና ዘላቂ ሀገራዊ ልማት አስተዋፅዎማድረጉን ያረጋግጣል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute