ኢንቪዲያ ኩባንያ 215 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማስመዝገቡን አስታወቀ፡፡
· AI Investment
Nvidia posts record $215.9 billion revenue as AI investment surge drives unprecedented growth.
የዓለማችንግዙፉ የኤ.አይ ቺፕ በማምረት የሚታወቀው ኢንቪዲያ ኩባንያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ላይ የሚደረገውኢንቨስትመንት እያደገ በመጣበት ወቅት የ215.9 ቢሊዮን ዶላር አመታዊገቢ በማስመዝገብ ክብረወሰን መስበሩን አስታውቋል።
ኩባንያውባለፉት ሶስት ወራት ብቻየነበረው የሽያጭ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይወቅት ጋር ሲነጻጸር በ73 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ይህም የኢኮኖሚተንታኞች ቀደም ብለው ከገመቱትበላይ መሆኑ ተመልክቷል።
የኩባንያውዋና ስራ አስፈጻሚ ጄንሰን ሁዋንግ እንደገለጹት "የኮምፒውተር ፍላጎት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ነው፤ ደንበኞቻችንም ለወደፊትእድገታቸው መሰረት ለሚሆነው የኤ.አይ ኢንዱስትሪ አብዮት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሱነው" ብለዋል።
ቢቢሲእንደዘገበው ኢንቪዲያ በአሁኑ ወቅት የ4.8 ትሪሊዮን ዶላር የገበያዋጋ በማግኘት በዓለም ላይ በግልጽ ከሚገበያዩ ኩባንያዎች ቀዳሚው ነው። ኩባንያውእንደ ኦፕን ኤ.አይ እና ሜታ ላሉ የቴክኖሎጂተቋማት ወሳኝ የሆኑ እና የላቁ ቺፖችንበማቅረብ የኤ.አይ መሰረተ ልማት ግንባታማዕከል ሆኗል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute