የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ቶኒ ብሌየር የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ::
· Visiting
Senior leaders from the Ethiopian Artificial Intelligence Institute and the Tony Blair Institute discussed strengthening cooperation to advance AI-powered public services and Ethiopia’s digital transformation.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ መስራች፣ ሊቀመንበር እና የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ቶኒ ብሌየር፤ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን እያዘመነ ስለመሆኑ በመናገር ተቋማቸው ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ሙሉ ቁርጠኝነት
ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው የቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ለመደገፍ እያደረገ ላለው አበርክቶ ምስጋና አቅርበዋል። ሁለቱ ተቋማት በኢትዮጵያ ያለውን የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ልማት እና ተግባራዊነት ለማረጋገጥ ቀጣይነት ባለው መልኩ በጋራ እንደሚሰሩም ተመላክቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute