አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለአፍሪካ አዲስ የለውጥ ሞተር እየሆነ ነው፡፡
· AI Solutions
Beyond the tech sector, AI is helping Africa address critical shortages in health, agriculture, and education, while raising urgent questions around data sovereignty, infrastructure, and long-term digital independence.
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ዘርፍን ከመቀየር ባለፈ በአህጉሪቱ የሚታዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን ለመፍታት እንደ ዋነኛ መሣሪያ ሆኖ እያገለገለ መሆኑ ተገለጸ። ቴክኖሎጂው በተለይ በጤና፣ በግብርና እና በትምህርት ዘርፎች የሚታዩ የባለሙያ እጥረት ችግሮችን ለመቅረፍ ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያሳየ ይገኛል።
በካሜሩን የያውንዴ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ፖሊን ሜላታጊያ እንደገለጹት ኤ.አይ ወረርሽኞችን ለመተንበይ፣ በሕክምና ምስል የታገዘ ምርመራ ለማካሄድ እና የሰብል በሽታዎችን ለመለየት ቀዳሚውን ሚና እየተጫወተ ነው። ይህም አፍሪካ የዘላቂ ልማት ግቦቿን እንድታሳካ ትልቅ አቅም ይፈጥርላታል።
ይሁን እንጂ የአህጉሪቱ የመረጃ ሉዓላዊነት አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል ያሉት ፕሮፌሰሩ መረጃን የተቆጣጠረ የወደፊቱን ይቆጣጠራል ሲሉ አስጠንቅቀው አፍሪካ ከዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት ጥገኝነት ለመውጣት የራሷን የዳታ ማዕከላት ማደራጀት እንዳለባት አሳስበዋል።
በመሰረተ ልማት ረገድ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት "Frugal AI" የተሰኘውና አነስተኛ ወጪ የሚጠይቅ የቴክኖሎጂ አማራጭ ለአፍሪካ ተመራጭ መሆኑ ተመልክቷል። አህጉሪቱ በሰው ኃይልና በመሠረተ ልማት ላይ በቂ ኢንቨስትመንት ካደረገች ኤ.አይን ለአፍሪካ ነፃነትና ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ መሣሪያ እንደሚሆን የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ዘገባ ያመለክታል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute