ከኮሪያ አድቫንስድ ኢንስቲትዩት ኦፍ ሳይንስ ኤንድ ቴክኖሎጂ የተዉጣጡ ልዑካን ኢንስቲትዩቱን ጎበኙ።
· Visiting
South Korean Delegation Explores Future Collaboration with EAII in AI Innovation
የልዑካን ቡድኑ በቅርቡ የተመረቀውን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤት፣ የኤ.አይ ስታርታፕ ማዕከል፣ የሮቦቲክስ ወርክሾፕ እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ ያለዉን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ልዑካኑ ኢንስቲትዩቱ የኤ.አይ ቴክኖሎጂን በተለያዩ ዘርፎች ተግባራዊ ለማድረግ እና በዘርፉ ያለዉን ሀገራዊ አቅም ለመገንባት እያከናወነ ላለው ተግባር አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
አክለውም ይህ ጉብኝት ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለሚኖራቸዉ የወደፊት ትብብር እንደ ወሳኝ መነሻ እንደሚያገለግል ጠቁመዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute