አምባሳደር ቼን ሃይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
· Visiting
Ambassador Chen Hai held discussions with EAII leadership on artificial intelligence research, digital transformation, and future Ethiopia–China collaboration in large-scale language models, computing capacity, and digital infrastructure.
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ የተመራ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አድርጓል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ልዑካኑን ተቀብለዉ አነጋግረዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ልማት እያከናወነ ያለዉን የምርምር እና ልማት ስራ አስመልክቶ ማብራሪያ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ ኢንስቲትዩቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መስክ እያከናወነ ላለው ውጤታማ ስራ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። አምባሳደሩ ቻይና በኤ.አይ ልማት እና ትግበራ ረገድ ያላትን ልምድም አጋርተዋል። ዓለም በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እንዲሁም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎች ላይ ፈጣን እድገት ዉስጥ ናት ብለዋል። አክለዉም ቻይና ኢትዮጵያ የራሷን ላርጅ ላንጉዌጅ ሞዴሎችን በማልማት፣ የኮምፒዩቲንግ አቅም ማጎልበት እንዲሁም አስቻይ መሠረተ ልማትን ለማልማት በቅርበት ለመስራት ዝግጁ መሆኑኗን ገልጸዋል።
ጉብኝቱ በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል በኤ.አይ ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ልማት ላይ አጋርነትን ለማጠናከር ትልቅ እርምጃ ይሆናል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute