ለስራ ፈጣሪዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የሚሰጥበት የቡት ካምፕ ስልጠና ተጀመረ።
· Other
EAII, AAU, and UNDP Launch AI Unipod Boot Camp to Equip Students and Startups with Practical AI Skills
ስልጠናው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ዩ.ኤን.ዲ.ፒ ጋር በመተባበር የሚያቀርበው ነው፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ለሰልጣኞች የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። ሰልጣኞች በስልጠናው የሚያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ ውጤታማ እንዲሆኑ አሳስበዋል። የሦስት ተቋማት ትብብር በሆነው ኤ.አይ ዩኒፖድ ስር የሚሰጥ የመጀመሪያው ስልጠና መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገውም ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስታርታፕ ማዕከል ኃላፊ ልብሰወርቅ ነጋሽ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሰልጣኞች ሀሳባቸውን ወደ ተግባር መለወጥ የሚችሉበትን ክህሎት በስልጠናው እንደሚያገኙ አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዲን ሽብሩ ተመስገን (ዶ/ር) በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሰልጣኞች ያገኙት እድል ወርቃማ በመሆኑ በአግባቡ እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል።
ይህ ስልጠና ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት በኢንስቲትዩቱ ዋና መ/ቤት የሚሰጥ ይሆናል። ቡት ካምፕ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለተማሪዎች እንዲሁም ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ክህሎትን እንዲላበሱ የሚሰጠው ስልጠና ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute