ሜታ እና ኤ.ም.ዲ የላቁ የኤ.አይ ስርዓቶችን ለመገንባት የሚያግዝ የ100 ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
· AI Investment
Meta signs $100 billion chip deal with AMD to expand AI infrastructure and reduce reliance on Nvidia.
ሜታ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ያለውን የበላይነት ለማረጋገጥ 100 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የቺፕ ግዢ ስምምነት ለኮምፒውተሮችና ለዳታ ሴንተሮች የሚያገለግሉ ፕሮሰሰሮችን እና ግራፊክስ ካርዶችን በማምረት ከሚታወቀው አድቫንስድ ማይክሮ ዲቫይሰስ (ኤ.ም.ዲ) ጋር ማድረጉን አስታወቀ።
ስምምነቱ ሜታ በኢንቪዲያ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስና የራሱን የላቀ አቅም ያላቸውን የኤ̣.አይ የግል ረዳቶች (Personal Superintelligence) ዕውን ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።
በስምምነቱ መሠረት ሜታ የ ኤ.ም.ዲ የቅርብ ጊዜ ውጤት የሆኑትን የMI540 ተከታታይ ጂፒዩዎች እና ሲፒዩዎችን በብዛት ይረከባል። ይህም ለዳታ ሴንተሮቹ 6 ጊጋዋት የሚጠጋ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀሙ ፕሮሰሰሮችን ለማቅረብ ያስችለዋል።
የሜታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ እንደገለጹት አጋርነቱ የሰውን ልጅ የዕለት ተዕለት ሕይወቱን በጥልቀት የሚረዱ እና አቅም የሚፈጥሩ የኤ.አይ ሥርዓቶችን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ወሳኝ እርምጃ ነው።
ቴክ ክራንች በድረገጹ እንደዘገበው ሜታ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በአሜሪካ የኤ.አይ መሠረተ ልማት ላይ 600 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ ማቀዱ ይታወሳል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute