ኢንስቲትዩቱ ለሌሎች ተቋማት ኩራትና አርዓያ መሆን እንደሚችል የመከላከያ መረጃ ኤሌክትሮኒክስ ዋር ፌር መምሪያ አባላት ገለፁ፡፡
· Visiting
Delegation Commends EAII’s AI Innovations as a Model of National Technological Progress.
የኢትዮጵያ መከላከያ መረጃ ኤሌክትሮኒክስ ዋር ፌር ኦፕሬሽን መምሪያ አባላት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋየ ዘውዴ ለጎብኚዎቹ ስለዋና መሥሪያ ቤቱ አጠቃላይ ገፅታ ገለፃ አድርገዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ በጤና፣ በግብርና፣ በፋይናንስ እና በሌሎችም ዘርፎች የሰራቸውን ስራዎች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ጎብኚዎቹ በበኩላቸው በጉብኝታቸውና በተደረገላቸወ ገለፃ ሀገራችን በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ምን ያህል እንደተጓዘች እንደተገነዘቡ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ ለሌሎች ተቋማትም ኩራትና አርዓያ መሆን የሚችል ተቋም መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
ጎብኚዎቹ የስታርታፕ ማዕከልን፣ ዲጅታል ቤተ መጽሐፍትን፣ የሆሎግራም እና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲሁም የኢንስቲትዩቱን የምርት ማሳያ ክፍል ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute