የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
· MOU
EAII and Agricultural Transformation Institute Sign MoU to Accelerate AI-Driven Agricultural Development.
ስምምነቱ ብግብርናው ዘርፍ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ዲጂታል ፈጠራ እና በዳታ ላይ የተመሰረቱ መፍትሔዎችን አጠቃቀም ለማሳደግ የሚያስችል የትብብር ማዕቀፍ ለመፍጠር ያለመ ነው።
በፊርማ መርኃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ግብርና የሀገራችንን ከፍተኛ ገቢ የሚሸፍን ዘርፍ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም ዘርፉን በኤ.አይ ቴክኖሎጂ በማገዝ ምርታማነትን መጨመር እንደሚቻል ገልጸዋል። ለዚህ አጋዥ የሆኑ የዳታ እንዲሁም የባለሞያ ድጋፍ ለማድረግ ኢንስቲትዩቱ ዝግጁ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በበኩላቸዉ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚሰራዉ ስራ ይህ ስምምነት አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል። ኢትዮጵያዊያን አርሶና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ ቀደም ሲል ያበለጸጋቸዉ ሲስተሞችን በማንሳት በቀጣይ የትኩረት ነጥቦች ላይ ዉይይት ተደርጓል።
ከስምምነቱ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ኢንስቲትዩቱን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute