“የAI ስልጠናን በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ማግኘት እድለኝነት ነዉ”
· Education
EAII and Partners Launch “AI for Government” Training in Dire Dawa to Build Digital Public Sector Capacity
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች እና የአይ.ሲ.ቲ ባለሙያዎች የኤ.አይ ክህሎት ማበልጸጊያ ስልጠና መስጠት ተጀመረ። በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ እና በዩኤን.ዲ.ፒ ትብብር የተዘጋጀ ነው።
ስልጠናዉን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ይታገሱ ደሳለኝ ሰልጣኞች ስለ ኤ.አይ ቴክኖሎጂ መሰረታዊ ግንዛቤ ለመጨበጥ የሚያስችላቸዉን እድል ኢንስቲትዩቱ ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር ማዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸዉ ስልጠናዉ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት በቴክኖሎጂ የበቃ የሰው ኃይል ማልማት ብሎም አሰራርን ለማዘመን ያግዛል ብለዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ኃላፊ መሃዲ መሐመድ (ኢንጅነር) በበኩላቸዉ ስልጠናው አቅምን ለማዳበር እና ሀገራዊ እድገትን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ያደርጋል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስታርታፕ ማዕከል ኃላፊ ልብሰወርቅ ነጋሽ (ዶ/ር) በበኩላቸው ስልጠናው በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የተደገፈ መሆኑን አንስተዋል።
"AI for Government’’ በሚል ርዕስ ለተከታታይ ሰባት ቀናት በሚቆየው ይህ ስልጠና መሰረታዊ የኤ.አይ ክህሎት፣ የዳታ ምንነትና ጠቀሜታ እንዲሁም ከቴክኖሎጂው ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ይዳሰሱበታል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute