ጉግል የጄሚናይ መተግበሪያን አዲስ ሞዴል ይፋ አደረገ፡፡
· AI Solutions
Google unveils Gemini 3.1 Pro with enhanced reasoning power as monthly users surpass 750 million.
ጉግል ከፍተኛ አቅም እንዳለው የተነገረለትንጄሚናይ 3.1 ፕሮ (Gemini 3.1 Pro) የተሰኘ የጄሚናይ መተግበሪያ አካልየሆነውን የኤ.አይ የቋንቋ ሞዴል አስተዋውቋል፡፡
ሞዴሉ የተነደፈው ቀላል መልስ ለማይገኝላቸው እና ጥልቅ ትንታኔ ለሚፈልጉ ተግባራት ሲሆን፤ መረጃዎችንአቀናጅቶ ወደ አንድ ወጥ ዕይታ የመቀየር አቅም አለው። አዲሱ ሞዴል በተለይ በአመክንዮአስተሳሰብ ላይ ትልቅ አቅም እንዳለው ኩባንያው አመላክቷል፡፡
ጄሚናይ 3.1 ፕሮ ሞዴል ከታናሹ ጀሚናይ 3 ሞዴል ከፍተኛ ማሻሻያ ተደርጎለትበተሻለ አፈጻጸም መቅረቡን የቴክ-ክረንች ዘገባ ያመለክታል፡፡በተለይም ውስብስብ በሆኑ የእውቀት ስራዎች እና የሞያ ተግባራት ላይ የላቀ አቅም እንዳለው ኩባንያው አስታውቋል።
ሞዴሉ አኒሜሽኖችንከመስራት ጀምሮ የአንድን ልብ-ወለድ ሥነ-ጽሁፋዊ ዘይቤ ወደ ዲዛይን እስከመቀየርየሚችሉ የፈጠራ ስራዎችን ማከናወን ይችላል።
ሞዴሉ በቅርቡ ለዓለማቀፍተጠቃሚዎች ክፍት እንደሚሆን ጉግል አስታውቋል።
የጀሚናይ መተግበሪያንበየወሩ የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር ከ750 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ዘገባው አስታውሷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute