የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
· MOU
The Ethiopian Artificial Intelligence Institute and the Adwa Victory Memorial have signed a memorandum of understanding to collaborate on using modern technology for historical preservation, capacity building, and innovation.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በስምምነቱ እንዳሉት ኢንስቲትዩቱ ከምስረታዉ ጀምሮ የተለያዩ ተቋማትን በቴክኖሎጂ ለማገዝ እየሰራ ነዉ ብለዋል። ዛሬ የተደረገዉ ስምምነት የነበሩንን ታሪኮች ለትዉልድ ማስተላለፍ እና በቴክኖሎጂው የበቃ የሰዉ ኃይል ለማፍራት አስቻይ ነዉ ብለዋል።
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ቤኮ (ዶ/ር) በበኩላቸዉ ሁለቱ ተቋማት አብረዉ መስራታቸዉ በተለይም መታሰቢያዉን በቴክኖሎጂ የዘመነ ለማድረግ በሚሰሩ ስራዎች ላይ አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል።
ሁለቱ ተቋማት የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን በጋራ ለመጠቀም፣ በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ብቁ ባለሙያ ለማፍራት ብሎም የሀገርን ታሪክ በሚገባዉ መልኩ በቴክኖሎጂ አስደግፎ ለመዘከር በሚያስችሉ ማዕቀፎች ዙሪያ በጋራ የሚሰሩ ይሆናል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute